(በእውቀቱ ሥዩም፤ የመ.ሳ.ቁ =የመልክት ሣጥን ቁጥር፤ 26119 ኮድ 1000)

የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ በውቀቱ ሥዩም ወደ ፌስቡክ ተመልሷል፡፡ በነገራችን ላይ“ የቁርጥ ቀን ልጅ” ማለት ቁርጥ በሚበላበት ቀን የተወለደ ልጅ ማለት ነው፡፡ ሌላ ትርጉም የለውም፡፡

ሰሞኑን በምትገምቱት ነገር ምክንያት ስለፖለቲካ ላልጽፍ ወስኛለሁ፡፡ ቀን እስኪያልፍ ስለ ወሲብ እየተማማርን እንቆይ፡፡
ለወንዶች፤
ከሴት ጋር ወሲብ ሲያደርጉ በፍጥነት ይጨርሳሉ ?ገንዘብዎትን ማለቴ ነው፡፡ መፍትሄው ቀላል ነው፡፡ በደመወዝ ማግስት በችቺኒያ በኩል አይንዱ፡፡
ግን የምር፤ ከፍቅረኛዎት ጋር ወሲብ ሲያደርጉ ለረጅም ጊዜ መቆየት ይፈልጋሉ? መፍትሄው ቀላል ነው፡፡ ሲወስቡ፤ ሌላ ነገር ያስቡ፡፡ ለምሳሌ ስለ ጸረ-ሽብር ሕጉ ያስቡ፡፡ ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያስቡ፡፡ ይህንን ካደረጉ በፍጥነት የሚረጩት እንባዎትን ብቻ ነው፡፡ ለፍተሻ ምኝታቤትዎ የሚገባው ፖሊስ “ለዛሬው ይበቃል “ብሎ ማጅራትዎትን ጨምድዶ እስኪያላቅቅዎ ድረስ ከፍቅረኛዎት ገላ ላይ አይወርዱም፡፡

አድንቁኝ ! ግዴላችሁም አድንቁኝ ! ጀግና ልበ ሙሉ መሳሪያ ተደቅኖብኝ እንኳን የማልፈራ ጓደኛችሁ ነኝ ......አድንቁኝ !!
.... አንድ ቀን በታሪክ ይች ፅሁፍ ታላቅነቷ ይወሳል ...አሌክስ ምናለ በሉኝ ቱ! አሁን ስፅፍላችሁ ሁለት ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ከግራና ቀኘ ተደግኖብኛል .... በድምሩ አራት የእጅ ቦንቦች ሁለት ጩቤወችና ሁለት የተጠቀለሉ ገመዶችም አሉ ......አንድ መገናኛ ሬዲዮም አጠገቤ ተቀምጦ ‹‹እሽሽሽሽ ወይራ አስራ ስድስት ...ሽሽሽ ቀበሮ ..ሰባት.......ሽሽሽሽ ድመቱ ተይዟል ›› የሚሉና ሌሎችም ድምፆች ያሰማል .....
እኔ ወንድማችሁ
የሽ ሰው ግምት የመቶ ምሳ
አንድ ብቻውን ውሃ እሚያነሳ .......ዘራፍ ........እፅፋለሁ ይሄ ሁሉ ሳያስፈራኝ .....

ኢትዮጵያ በህወሓት ታማኝነት መስፈርት ብቻ ሰዎች ያለሞያቸው የሚያመሰቃቅሏት ሀገር ናት።
የዛሬው ተሿሚ ወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳንን ለአብነት እንመልከት።
ሰውዬው የድህንነት ሰው ነበር። የ6 ዓመት የአፈና እና ግድያ ብቃቱ ፍትሕን ለማጉደል ብቁ ሆኖ በመገኘቱ የኦሮሚያ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ እንዲሆን ወንበሩ ተቸረው።
ከዚያ በፍትሕ ላይ የነበረው የጭካኔ ስብእና ህወሓቶችን በማስጎምጀቱ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ሆኖ እንዲሰራ ተመደበ።
እንደተገመተው በፖሊስ ኮሚሽነርነት ስልጣን ዘመኑ በተለይ በምርጫ 97 በነበረው ጭፍጨፋ የሟቹ መለስን ትእዛዝ በዋነኛነት ያስፈጸመ ኮከብ ነፍሰ ገዳይ በመሆን የደኅንነት መስሪያ ቤት ልምዱን በፖሊስ ቤት አሻራውን አሳረፈ።
(ከ11 ዓመታት በፊት በዛሬው ዕለት ጥቅምት 22,1998 በፖሊስ ኮሚሽነርነት የአዲስ አበባ ሕዝብ ላይ ለፈጸመው ጭፍጨፋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ስጦታ ተበርክቶለታል::)

ኢህአዲግ ሥራውን አልሰራም ብሎ ጌታቸው ረዳ ሲያዝን ሰምቼው ነበር ፤ እውነቱን ነው!!! ሕዝቡ ደምህ ደሜ ነው እየተባባለ ሲደጋገፍ ስላየሁ ፤ አሁንም መደጋገፉን አላቋረጠም። ነገር ግን ተማርን ፣ አውቅን ፣ እኛ ከህዝቡ ስለምንሻል እንመራዋለን ባይ የፖለቲካ ቡድን መሪዎች ላይ ግን ብዙም ሳይድክም ውጤታማ ሥራ መሥራቱን ከሰሞኑ ተመልክተናል።

ቅድሚያ ለኢትዮጵያ ብዬ ይህን ጽሁፍ ስክትብ ፤ ወፍ ዘራሽ እና ዘር አልባ ሆኜ ሳይሆን ፤ እንደ ዘመኑ እና ዓለም በደረሰበት የአስትሳሰብ ደርጃ የወቅቱን የፖለቲካ ግለት መመልከት ስላለብኝ ነው።

ኢትዮጵያን “ኢትዮጵያ” አሰኛት የዘመኑ ልሂቃን (?) ከሚያቁት የ100 ዓመት ታሪክ በላይ ልቆ ለ3000 ዓመታት የዘለቀውን የአብሮነት እና በጋራ የሀገርን ዳር ድንበር የማስጠብቅ ሥራ ከ80 በላይ ብሄሮች ሥራ እንጂ የአንድ ብሄር ሥራ እንዳልነበር ታሪክ ስለመዘገበልን ነው።

ስለ ኢትዮጵያ ሳወራ ስለ 4 እና 5 ብሄር አላወራም ከ80 በላይ ብሄሮችን ስለያዘው ህብር እንጂ። የመለስ ዜናዊ እና ኢህአዴግ ህልም ሀገሪቷን በዘር በትኖ የትግራይ ኢምፓየርን መገንባት ነበር ፤ እነርሱ ሲያቅታቸው ግን ተተኪ አግኘተዋል። ስለዚህ ውጊያችን እየወደቀ ካለው ኢህአዴግ ጋር ብቻ ሳይሆ አለን አለን ከሚሉት ከነዚህ ልሂቃንም(?) ጋር ነው።

የኢሊባቡር ጎሬ ልጅ ናቸው። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር መስራች ከነበሩት ጥቂቶች መካከል። ኦነግ ከሕወሃት የጋራ መንግስት መስርቶ የነበረ ጊዜ የማስታወቂያ ሚኒስትር በመሆን ለትንሽ ጊዜ ሰርተዋል። ዶር ጊማ ነግዎ ይባላሉ። የተከበሩ ሰው።

ከአቶ ሌንጮ ለታ፣ ሌንጮ ባቲ፣ ዶር በያን አሴቦ ካሉ አንጋፋ የኦሮሞ ታጋዮች ጋር የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር (ኦዴፍ) መስራችና ከፍተኛ አመራር አባል ናቸው። ኦዴፍ በተለያየ ጊዜ አቋሙን እንደገለጸው የመገንተ ጥያቄ ያለፈበትና አይረጀ፣ የኦሮሞዎችን ጥያቄ የሚመለስ ብቻ ሳይሆን የኦሮሞዉን ማህበረሰብ የሚጎዳ እንደሆነ በመናገር፣ ሉዓላዊነቷ በተጠበቀ በአንዲት ኢትዮጵያ ሥር፣ የሁሉም ዜጎች መብት የተከበረባት፣ ሁሉም እኩል የሆኑባት ኢትዮጵያን ለመገንባት ቆርጦ የተነሳ ድርጅት ነው። የኦሮሞ ጥያቄ ከሌላው ጥያቄ ግር አንድ እንደሆነ ብዙ ጊዜ የሚናገሩት የኦዴፍ አመራር አባላት፣ ዴሞክራሲኦያዊ ስርዓት ከተገነባ ያሉ ልዩነቶች በሙል ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ሊፈቱ ይችላሉ ብለው ያምናሉ።

ይቺ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ስንት የመከራ ወንዞችን ተሻግራለች! ገና ስንት ትሻገራለች! ስንት የግፍ ተራራዎችን አቋርጣለች! ገና ስንት ታቋርጣለች! ስንት የበደል ሰይፎችንና ጦሮችን አምክናለች! ገና ስንት ታመክናለች! ስንት የውጭ ኃይሎችን አሳፍራለች! ገና ስንቱን ታሳፍራለች! ስንት አምባገ- ነኖችን እያለቀሰች ቀብራለች! ገና ስንቱን ትቀብራለች! ጭቆና ከኢትዮጵያውያን ደም ሙልጭ ብሎ ወጥቶ በነፃነት፣ በእኩልነት፣ በዳኝነት በጠራ ደም እስቲተካ ድረስ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ዘርግታ ትጸልያለች! እግዚአብሔርም ቃል ኪዳን አለበት ይሰማታል! የኃያላን ኃያል ኢትዮጵያ እንድትፈርስ አይፈቅድም!
የኢትዮጵያን መፈራረስ የሚመኙ ግለሰቦችም መንግሥቶችም ሞልተዋል፤ ኢትዮጵያ እንድትፈራርስ የሚመኙ ጭንጋፍ ልጆችም አሏት፤ ማኅጸንዋ እየደማ እየረገማቸው ሰላምና እንቅልፍ አጥተው አብጠው ይፈነዳሉ፤ የኢትዮጵያን መፈራረስ የሚመኙ መንግሥቶች ሁሉ ከዚህ በፊት ቀድመው ፈራርሰዋል፤ ወደፊትም ይፈራርሳሉ።