ቢያንስ ለቅሷችንን እንኳ በጋራ እናልቅስ - አክቲቭስትና አርቲስት ታማኝ በየነ

ቢያንስ ለቅሷችንን እንኳ በጋራ እናልቅስ - አክቲቭስትና አርቲስት ታማኝ በየነ

ጽናት የውውይት መድረክ በሚኒሶታ ባዘጋጀው ሁሉን ያካተተ የውይይት መድረክ ላይ ተወዳጁ አክቲቭስትና አርቲስት ታማኝ በየነ ተገኝቶ ተሰብሳቢውን እምባ ያራጨ ንግግር አድርጓል:: በዚህ ዝግጅት ላይ ከጋምቤላ; ከኦጋዴን; ከኦሮሞና ከአማራ የተወከሉ ተናጋሪዎች የነበሩ ሲሆን በሕዝባችን ዘንድ ያለውን አንድነት ለማጠናከር ወይም በአንድ ላይ ለመጓዝ ሁኔታዎችን ያመቻቹ ንግሮች ተደርገዋል:: ታማኝ በየነ “ቢያንስ ለቅሷችንን እንኳ በጋራ እናልቅስ” ሲል ስለአንድነትና መተባበር አስፈላጊነት ያደረገውን ንግግር ቢያድምጡት ይጠቀማሉ:: (ዘ-ሐበሻ)